የነፍስህ
ጥሪ ዝምታህ
ሁለት ቀለማት ተቦሻሽረው
አዲስ ቀለም ቅይጥ ወልደው
ከትንፋሽ እስትንፋስ ስጦታ በቀር
የኑሮህ ትርጉም ለዚች ምድር
ላባት እናት ላክፋሌ ስልሰት
ቅልቅሉ የተፈጠርክበት
ሽተህ ነበር ያኔ ዓለምን ስታያት
የሲኦል ርጋታ ቆቡን የደፋባት
ባልሰከነው ድስቷ
ከላይ በመርጋቷ
ውስጡን ለሚበላህ
ንገረው ተለየው ዘላለም ሚያኖረህ የነፍስ ጥሪ አለብህ ፡፡
/አርአያ መካሻ 26/07/05ዓ.ም./