Saturday, April 28, 2012

ሲዳማ

ሲዳማ…..


አንዱ ካንዱ ባሻገር
ከጥልፉ ከወንዙ ዳር
ከማደስ ውልደት ጥግ
የባልደራሱ ማደግ
ያንተነትህ ክታብ እውነት
ሁለት ሲሆን ያንተ ውስጠት
ከኮከቡ ሻግራ ከሰማይ ጥቁረት ድምቀት
የብርሀን ፀዳል አይደል የምታየው እውነት                                                  
ሁለትነት በልዩነት ብርሃንህ በጭለማ
የዘመናት ኑረት ትርቀት አይደል ያሳለፍከው ኑሮ ዜማ
ባትደንስ ባትቦርቅ ‘ንኳን
ባታዝንም ባትከፋ ‘ንኳን
ሁለትነት ላንተ አንድ አይደለም
ህይወት ሲዳማ እንጂ ትርቀቱ ሌላውማ የመኖርህ ትርጉም የለም ፡፡



 አርአያ መካሻ/ቺምፑ /ዛሬ1/8/04

እንዲህ ተጀመረ


                                       የእሾሀማው ፍሬ

አዳም እንዲበላ ባታቀብል ኖሮ
እሷም ባታዳምጥ ይህ እንዳይሆን ድሮ
ሄዋኔ ጥናቴ አዳኝ መድሀኒቴ
የጎኔ ስብራት ጠጋኝ ነሽ ህይወቴ
ግና አሁን ገና 
ብነቃ እንደገና 
አንቺንም ባልኮነንኩ
በራሴው መስጠቴን ይናገሩ ነበር የገዛ እጆቼ
ያኔ ታዲያ ምን እል ነበር አግዢኝ ወዳጄ
ተራው በሁላችን አንድ አንድ አይነት ከነበር 
ወቃሽና ተወቃሽ ባንሆን አይሻልም ነበር

 አርአያ መካሻ