Monday, April 8, 2013

ጉዳችንን ዝም ብለን እያየነው ነው


ሁለት ነገሮችን እናስደምጥ ……  ምንድነው ዝምታው ግን   መተሐራ እኮ በመስጠም ላይ ነች ……ኤጭ …ወዲያ ም  ማላዘን  ነው  …በዓለማችን ላይ ከምንሰማቸው  እጅግ አስደንጋጭ ታሪኮችን  ኢትዮጵያ ልታስተናግድ  እየሆነ  ለምንድነው  ተወጆቹ  ልጆቻ  ዝምታን የመረጥነው …….  በሰቃው  እኮ  የመተሀራ

 ፤ አዲስ ከተማ ፤ መርቲ መንገድን 

እየዘጋው ነው  
ግን ዝም ተብላል  በተጨማሪ …..  አዲስ ከተማ ያሉ ቤቶች  እየገባባቸው  ነውኮ  ሰውም መንግስትም ዝም ነው  ወይስ  እየተሰራ ያለውን ዝምታ እናስጩኸው 

Thursday, April 4, 2013

የውልደትህ ክዳን


የነፍስህ ጥሪ ዝምታህ

ሁለት ቀለማት ተቦሻሽረው
አዲስ ቀለም ቅይጥ ወልደው
ከትንፋሽ እስትንፋስ ስጦታ በቀር
የኑሮህ ትርጉም ለዚች ምድር
ላባት እናት ላክፋሌ ስልሰት
ቅልቅሉ የተፈጠርክበት
ሽተህ ነበር ያኔ ዓለምን ስታያት
የሲኦል ርጋታ   ቆቡን የደፋባት
ባልሰከነው ድስቷ
ከላይ በመርጋቷ
ውስጡን ለሚበላህ
ንገረው ተለየው ዘላለም ሚያኖረህ የነፍስ ጥሪ አለብህ ፡፡

/አርአያ መካሻ 26/07/05ዓ.ም./

Saturday, April 28, 2012

ሲዳማ

ሲዳማ…..


አንዱ ካንዱ ባሻገር
ከጥልፉ ከወንዙ ዳር
ከማደስ ውልደት ጥግ
የባልደራሱ ማደግ
ያንተነትህ ክታብ እውነት
ሁለት ሲሆን ያንተ ውስጠት
ከኮከቡ ሻግራ ከሰማይ ጥቁረት ድምቀት
የብርሀን ፀዳል አይደል የምታየው እውነት                                                  
ሁለትነት በልዩነት ብርሃንህ በጭለማ
የዘመናት ኑረት ትርቀት አይደል ያሳለፍከው ኑሮ ዜማ
ባትደንስ ባትቦርቅ ‘ንኳን
ባታዝንም ባትከፋ ‘ንኳን
ሁለትነት ላንተ አንድ አይደለም
ህይወት ሲዳማ እንጂ ትርቀቱ ሌላውማ የመኖርህ ትርጉም የለም ፡፡



 አርአያ መካሻ/ቺምፑ /ዛሬ1/8/04

እንዲህ ተጀመረ


                                       የእሾሀማው ፍሬ

አዳም እንዲበላ ባታቀብል ኖሮ
እሷም ባታዳምጥ ይህ እንዳይሆን ድሮ
ሄዋኔ ጥናቴ አዳኝ መድሀኒቴ
የጎኔ ስብራት ጠጋኝ ነሽ ህይወቴ
ግና አሁን ገና 
ብነቃ እንደገና 
አንቺንም ባልኮነንኩ
በራሴው መስጠቴን ይናገሩ ነበር የገዛ እጆቼ
ያኔ ታዲያ ምን እል ነበር አግዢኝ ወዳጄ
ተራው በሁላችን አንድ አንድ አይነት ከነበር 
ወቃሽና ተወቃሽ ባንሆን አይሻልም ነበር

 አርአያ መካሻ