Thursday, April 4, 2013

የውልደትህ ክዳን


የነፍስህ ጥሪ ዝምታህ

ሁለት ቀለማት ተቦሻሽረው
አዲስ ቀለም ቅይጥ ወልደው
ከትንፋሽ እስትንፋስ ስጦታ በቀር
የኑሮህ ትርጉም ለዚች ምድር
ላባት እናት ላክፋሌ ስልሰት
ቅልቅሉ የተፈጠርክበት
ሽተህ ነበር ያኔ ዓለምን ስታያት
የሲኦል ርጋታ   ቆቡን የደፋባት
ባልሰከነው ድስቷ
ከላይ በመርጋቷ
ውስጡን ለሚበላህ
ንገረው ተለየው ዘላለም ሚያኖረህ የነፍስ ጥሪ አለብህ ፡፡

/አርአያ መካሻ 26/07/05ዓ.ም./

No comments:

Post a Comment